የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ ምንጣፎች ወዘተ---ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ኢአጽ/ግንአዳ/006/2018
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ ምንጣፎች ወዘተ---ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች፤
-
- የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለገሃር ከሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በመሙላት ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ2፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ መነሻውን 20% (ሃያ በመቶ) ሲሆን ዝቅተኛው የማስያዣ ዋጋ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) በሚል ሥም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለአንድ ዓይነት ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ዕቃዎች መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሆኑበትን የዕቃ ዓይነት አጠቃላይ ዋጋውን በአስራ አምሰት ቀናት ውስጥ በመክፈል በአለበት ሁኔታ ተረክበው መውሰድ አለባቸው። ክፍያውን ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሆኑት ዕቃ ክፍያ የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ጨረታው ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መሥሪያ ቤት ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
