በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አገልግሎት የሚውል ከብረት የተሰራ ዘመናዊ የዶሮ ኬጂ ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 08/2018
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አገልግሎት የሚውል ከብረት የተሰራ ዘመናዊ የዶሮ ኬጂ ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. ዘመናዊ የዶሮ ኬጂ ግዥ በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደስ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።
- ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
- ለሚወዳደሩባቸው የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ አቀራረብ፣ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አሰ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ፡- 0115548264/011869-43-66
የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ጽ/ቤት
