ዳሽን ባንክ በብድር ለሚይዛቸው የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን እና ማሽነሪዎችን ማቆያ የሚሆን ስፋቱ ከ 1000 – 3000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን አጥር ግቢ እና በውስጡ ደረጃውን የጠበቀ መጋዘን እንዲሁም የጥበቃ ቤት ያለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ ቦታ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
DASHEN BANK S.C (ዳሽን ባንክ አ.ማ)
ዳሽን ባንክ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር DBOTO7025/26
ዳሽን ባንክ በብድር ለሚይዛቸው የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን እና ማሽነሪዎችን ማቆያ የሚሆን ስፋቱ ከ 1000 – 3000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን አጥር ግቢ እና በውስጡ ደረጃውን የጠበቀ መጋዘን እንዲሁም የጥበቃ ቤት ያለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ ቦታ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ።
- ለጨረታ የሚቀርብ ማንኛውም ተወዳዳሪ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርቴፊኬት ወይም ካርታ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ ፈቃዱም በዘመኑ የታደሰ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት (Tax Payer Registration Certificate) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት (Valu Added Tax registration Certificate) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለ90 (ዘጠና) ቀናት የሚቆይ በዳሸን ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ፣ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) እና የጨረታ ሰነድ (የዋጋ ማቅረቢያ) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በተራ ቁጥር 6 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በማግስቱ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
ዳሽን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት
ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት
ሰፕላይቼን ማኔጅመንት መምሪያ 7ኛ ፎቅ
7. ባንኩ ተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-115-180356 ኤክስቴንሽን 3158 ወይም 3159 መደወል ይቻላል፡፡
ዳሽን ባንክ አንድ እርምጃ ቀዳሚ !
