ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ ለቧንቧ ውሃ ዝርጋታ የሚውሉ HDPE Pipe and Fitting በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሸቲቭ በቦረና ዞን በትግበራ ላይ ካሉት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ በSOS በተገኘው ድጋፍ የሚተገበር "Integrated Response to Malnutrition (IRM) through Agricultural, Health, Nutrition, and WASH Interventions” የሚል ፕሮጀክት ነው:: ስለዚህም ድርጅታችን በቀሌም ወለጋ ዞን በጋዮ ቄቤና በዳሴ ዋቤራ ወረዳዎች ህብረተሰቡን የንፅህናና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል:: በመሆኑም ለቧንቧ ውሃ ዝርጋታ የሚውሉ HDPE Pipe and Fitting በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህም በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያሳችሁና የጨረታውን ሰነድ መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢ የንግድ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን 300 ብር በመክፈል ከድርጀቱ መግዛት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በሁንዴ ግራስሩትስ ዲቬሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መስቀል ፍላወር አካባቢ ያሬድ ቤ/ክ ጀርባ በሚገኘው ዋና መ/ ቤት ማቅረብ ይችላሉ።
የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ቅፅ የሚጠናቀቀው ከላይ በተገለፀው መሠረት በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሚከፈተው በዚያው ቀን 4:30 ላይ ይሆናል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር :- 011 558 40 94 /0913399817 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
