የሰሃላ ሰየምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስ/ር ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው መደበኛ በጀት አሰ/ር ሎት-1 በስ/ሰ/ወ ግብርና ጽ/ቤት አማካኝነት በአቅኝ ቀበሌ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋም (ኤፍቲሲ) ግንባታ እና ሎት-2 በስ/ሰ/ወ ትም/ት ጽ/ቤት አማካኝነት በፍነዋ ቀበሌ ባርጫኔ ከተማ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት ኮሎን ቁሞ የተቋረጠ ግንባታ ስራ ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ግንባታውን ማስገንባት ወይም ማሰራት ይፈልጋል።
የሰሃላ ሰየምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰሃላ ሰየምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስ/ር ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው መደበኛ በጀት አሰ/ር ሎት-1 በስ/ሰ/ወ ግብርና ጽ/ቤት አማካኝነት በአቅኝ ቀበሌ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋም (ኤፍቲሲ) ግንባታ እና ሎት-2 በስ/ሰ/ወ ትም/ት ጽ/ቤት አማካኝነት በፍነዋ ቀበሌ ባርጫኔ ከተማ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት ኮሎን ቁሞ የተቋረጠ ግንባታ ስራ ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ግንባታውን ማስገንባት ወይም ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ከስራው ጋር ተያያዥ የሆነና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸው፤
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባችሁ፤
- ተጫራቾች በኤፍቲሲ ግንባታው ለመሳተፍ በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ-9 እና ከዚያ በላይ ወይም በህንጻ ስራ ተቋራጭነት ከደረጃ-10 እና ከዚያ በላይ ሲሆን እንዲሁም በትም/ቤት ግንባታ ለመሳተፍ በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ ወይም በህንጻ ስራ ተቋራጭነት ከደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የሚያገለግል የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ የሚገባ ሲሆን ተጫራቹ ዋጋ ከሚሞላው ሰነድ ላይ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ወይም ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ኦርጅናል እና ሌሎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠየቁትን ዝቅተኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንስ ግምገማው የሚያልፉ ይሆናሉ።
- የግንባታውን የስራ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከስ/ሰ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ወይም መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 /ሰላሳ/ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ31ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ከተጫራቾች መካከል አሸናፊው ለሆነው ድርጅት ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 /አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ/ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ በግዥ ማስፈጸሚያ መመሪያው በተፈቀዱት የውል ማስከበሪያ ማስያዣ አይነቶች በአንዱ በማስያዝ በአካል በመቅረብ ውል መውሰድ አለበት።
- የጨረታውን የበለጠ ዝርዝር መረጃ እና መስፈርቶች ለማወቅ ከተጫራቾች መመሪያ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥም ጨረታውን ካወጣው መ/ቤት ጋር ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ቀን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0927223012፣ 0935387575 ፣ 0902126041 ወይም 0918317663 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- መሸሃ ከተማ ስ/ሰ/ ፖሊስ ጽ/ቤት ዝቅ ብሎ
የሰሃላ ሰየምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
