በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ
- በተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በተሰማሩበት ዘርፍ ብቻ ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ በኮፒ ሰነዱ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ሰነድ 200.00 ብር የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ በግንባር በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላደረገ ስርዝ ድልዝ ያደረገ አማራጭ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀኑ በአል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 04 ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ጎተራ ኮንደሚኒየም ሙሉ ወንጌል ቸርች አጠገብ
ስልክ:- 011 8 68 18 24/20
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ
