Tender Detail

Tender Details

  • Company የምስራቅ ስልጤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጤ ወረዳ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0925109200
  • Website
  • Deadline02 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለሎት1. አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000) እና ለሎት 2. ሀምሳ ሺህ ብር (50,000)
  • opening date2026-01-02 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Construction Works , Contractors

በ2018 በጀት ዓመት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጤ ወረዳ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የምስራቅ ስልጤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በ2018 በጀት ዓመት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጤ ወረዳ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው ለሎት 1. G.C-9/ B.C-9 ለሎ-ት.2. G.C-9/ B. C-9 R.C-9 እና ከዛ በላይ የሆኑ ፡-

ሎት 1. ገርቢበር ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማስገንባት

ሎት 2. አዳሳ ማዘጋጃ ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ኮብልስቶን ማንጠፍ

  • የዘመኑ ግብር አጠናቆ የከፈሉ ፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤
  • የታደሰ የንግድ ፍቃድ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የሥራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ለሎት1 አንድ መቶ ሺህ ብር 100,000 ለሎት 2. ሀምሳ ሺህ ብር (50,000) የጨረታ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፤
  • የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሥሯቸውን ሥራዎች የሚገልፅ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ከምስራቅ ስልጤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ፤ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ምስራቅ ስልጤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ-

ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል። የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም።

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0925109200፣ 0929947257፣ 0929938904፣ 0939330829

 

የምስራቅ ስልጤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender