Tender Detail

Tender Details

  • Company Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)
  • Address ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት አጠገብ ዋስትና የንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-11-23-13
  • Websitehttps://psssa.gov.et/
  • Deadline28 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Billboards And Digital Advertising , Spare Parts , Electronics Materials

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የLED Screen እቃውን ከነመግጠሚያው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የLED Screen እቃውን ከነመግጠሚያው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

ሎት 1. የLED Screen ከነመግጠሚያው

ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ክሊራንስ) ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡:

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ የማይመስስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ፊት ለፊት የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 313 መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በመሙላት የቴክኒካል እና ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ የፋይናንሽያል ሰነድ በኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313 ማስገባት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጨረታ ማስከበሪያ የብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
  2. ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 313 ነው። 16ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  3. አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ ቁጥር- 0111 23 26 99

 

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Save Tender