Tender Detail

Tender Details

  • Company Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ወርቁ ሰፈር (ውሃ ልማት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ መስጊዱ እካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 17 51 51
  • Websitehttps://www.dce-et.com/
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Spare Parts

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለተለያዩ ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች (Spare Parts) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/ SP/184/2025

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለተለያዩ ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች (Spare Parts) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 

የዕቃው አይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

Spare Parts

ዋና መ/ቤት

DCE/Sp/184/2025

ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም 5:00 ሰዓት

ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም 5፡15 ሰዓት

50,000.00

 

ስለሆነም ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

E-mail አድራሻ Info@dce-et.com የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com

ፖ.ሳ.ቁ 3414

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender