የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የክልል ኤርፖርቶች፡- ጂንካ፣ ጎዴ፣ አክሱም፣ አርባ ምንጭ፣ ቀብሪ ደሀር፣ ላሊበላ እና ጋንቤላ ኤርፖርቶች የአጥር ግንባታ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላና የህንጻ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T592
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የክልል ኤርፖርቶች፡- ጂንካ፣ ጎዴ፣ አክሱም፣ አርባ ምንጭ፣ ቀብሪ ደሀር፣ ላሊበላ እና ጋንቤላ ኤርፖርቶች የአጥር ግንባታ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላና የህንጻ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ በሀገር ውስጥ የተመዘገቡና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግሥት ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T592 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ፣ የጨረታ ቁጥር፣ የድርጅቱን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ 180 ተከታታይ ቀናት ነው።
ተጫራቾች አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ፣ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150ቀናት የሚቆይ መሆን ይኖርበታል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል እሰከ ጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ9፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ፕሮኪዉርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት-
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል
በስልክ ቁጥር: +251-115-17 4552
ኢ-ሜይል: AIiAs@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
