በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የአጥር ጥገና፣ የህንፃ እድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል
ለሁስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የአጥር ጥገና፣ የህንፃ እድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንጋብዛለን፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ።
1.በሙያው ዘርፍ (በሚመለከተው በንግድ ስራ) የተሰማራና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው (ያላቸው) እና የ2017ዓ/ም ሙሉ ግብር ከፍሎ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ያላቸው::
3. የግዥ መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ብርና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራቁጥር1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታችሁን ማስረጃ ፎቶ ኮፒና ኦርጅናል ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5 የእቃውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በናሙናው መሰረት ማቅረብ የሚችል /ናሙናውን ከመ/ቤቱ ማገኘት ይችላል፡፡
7. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ በመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱ ላይ ቫትን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመልስ 200ብር (ሁለት መቶ) ብር እየከፈለ ከደቡብ ወሎ ዞን ከለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆ/ል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 41 መግባት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢል ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ የባንከ ዋስትና ከሆነ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡
10. የውል ማስከበሪያ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ 10 % ማስያዝ የሚችል፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸት ፖስታ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት( ባአየር) ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን ድረስ በጥንቃቄ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ማህተም በማድረግ እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል ፡፡የጨረታ ሳጥኑ 5፡15 ላይ ይታሸጋል፡፡
12. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ5፡30 ላይ ይከፈታል ፡፡ተራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
13. ጨረታው በሎት (በጥቅል ዋጋ) የሚወዳደር ይሆናል፡፡
14. እቃው ገቢ የሚሆንበት ቦታ ደቡብ ወሎ ዞን አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ነው፡፡
15. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
16. ተጫራቾች በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የስራ ዘርፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢፈልግ አቀስታ ጠቅላላ ሆ/ል ቢሮ ቁጥር 36 ድረስ በአካል በመኘት (ቢሮ በስልክ ቁጥራችን 0331140366/09 27403736/0915541090 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ
- ሆ/ሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች አቤቱታ ካላቸው ውጤቱ በተገለፀ በተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ላወጣው ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት በጽሁፍ ማቅረብ አለበት፡፡
- ሁሉም ጨረታ በሎት/በድምር ዋጋ የሚወዳደር ይሆናል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ጠቅሳሳ ሆስፒታል
