የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሞተርሳይክል L no cc በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሞተርሳይክል L no cc በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
➢ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
➢ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ 10,000 (አስር ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
➢ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
➢ የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4:30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
➢ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በ5ኛው የስራ ቀን ከላይበተጠቀሰው ቦታ ከቀጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 5፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
➢ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
➢ ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቶች ይሆናል፡፡
➢ አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ሁተኛ ፎቅ በስተግራ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
