በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ለእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለከተማ አስተዳደሩ የውስጥ ለውስጥ ጠጠር መንገድ ለማሰራት / ስለተፈለገ ማሽኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ለእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለከተማ አስተዳደሩ የውስጥ ለውስጥ ጠጠር መንገድ ለማሰራት / ስለተፈለገ ማሽኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና ከዚያም በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገበ እና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድቦንድ/ 75,000 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት የሚቆጠር እስከ 22ኛው ቀን ከጠዋት 3፡00 ሶስት ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ሰዓት ከሰላሳ አንድ ተዘግቶ 4፡00 አራት ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ንብ/አስቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል።
- የዕቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላል። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 የሰነድ ክፍያ በመፈጸም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ ንብ/አስቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሔራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል።
- የጨረታው ተሳታፊዎችን ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙሊያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ማቴሪያሎች እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ባዘጋጀው ሳይት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል ጽ/ቤት
