Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሰንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና የኮምፒወተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ልዩ ልዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 07-2018

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሰንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና የኮምፒወተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ልዩ ልዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ እድሜው ከ18 በላይ የሆነ ከተሸከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተ/ቁጥር 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታውን መሳተፍ ይችላል፤
  3. ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ -ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም አያስፈልግም፡፡
  4. የሐራጅ ጨረታው ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል፡፡
  5. ተጫራቾች ለሐራጅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ገቢ ሂሳቦች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 207 አስከ ጨረታው ቀን ታህሳስ 07 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ድረስ ማስያዝ አለባቸው።
  7. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  8. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
  9. ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጠት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፤
  10. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉብትን ዕቃ ዋጋ 5 1 በአምስት/ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፤
  11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተግለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ማንሳት ያልቻለ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፣
  12. በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስም ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም፤
  13. ተሸከርካሪው ማህበራዊ ታክስ የሚመለከተው ከሆነ ከሚሰጡት ዋጋ ላይ 3% የማህበራዊ ታክስ የሚከፍል ይሆናል።
  14. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውዏ መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
  15. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

 

ተጫራቾች በሐራጅ ጨረታ ወይም ደግሞ ለሽያጭ የወጡ ዕቃዎችን በተመለከተ ጥያቄ ካስ በስልክ ቁጥር 058-320-74-18/058-320-75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender