Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security100,000.00 (መቶ ሺ ብር)
  • opening date2025-12-22 00:00:00
  • Categories Consultancy Service

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የመጀመሪያ ዙር የህዝብ ሽያጭ ዝግጁነት ምክር አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ምክር አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: ECMA/NCB/12/2018

 

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የመጀመሪያ ዙር የህዝብ ሽያጭ ዝግጁነት ምክር አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ምክር አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር በመክፈል ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን፤ እንዲሁም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነደ ሙዋለንዋይ ኢቨስትመንት አማካሪ ፍቃድ ያገኙ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  5. ጨረታው ሀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው።
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
  7. አሸናፊው ተጫራች የምክር አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ ሁሉ በራሱ ትራንስፖርት ባለስልጣኑ ዋ/መ/ቤት ወይም የምክር አገልግሎቱ በሚካሄድባቸው ሌሎች ቦታዎቸ ሁሉ የመገኘት እና የምክር አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት።
  8. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 100,000.00 (መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  10. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  11. ጨረታው ታሀሳስ 13 ቀን 2018 ከሰዓት በ9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ9:30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  12. በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
  13. ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት

ምናዬ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርክ፣ ክ/ከተማ ቂርቆስ፣ ወረዳ 9 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ 011-5-57-83-27

ኢሜል፡ Procurement@ecma.gov.et

 

Save Tender