በፐብሊከ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት በደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የህንጻ ተቋራጮችን በሸገር ከተማ አስተዳደር የካ ጣፎ ክ/ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚሰሩ ሎት 01 ኤካ ወረዳ ፣ ሎት 02 ለገዳዲ ዳሌ ወረዳ እና ሎት 3 ደምበል ጣፎ ወረዳ የሦስት አቅመ ደካማ ቤቶች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በፐብሊከ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት በደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የህንጻ ተቋራጮችን በሸገር ከተማ አስተዳደር የካ ጣፎ ክ/ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚሰሩ ሎት 01 ኤካ ወረዳ ፣ ሎት 02 ለገዳዲ ዳሌ ወረዳ እና ሎት 3 ደምበል ጣፎ ወረዳ የሦስት አቅመ ደካማ ቤቶች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ የሥራ ተቋራጮች ማሟላት ያሉባቸው መመዘኛዎች፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- በግንባታ ውለታ ገብተው ባላቸው ደካማ አፈጻጸም የተነሳ ውለታ ያልተቋረጠባቸው እና ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው የሥራ ተቋራጮች።
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በኮንሰትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ሥራ ተቋራጮች እና ኮንትራክተሮች ሆነው በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በእጃቸው ምንም አይነት ሥራ እንደሌላቸው ወይም 70% አፈጻጸም ላይ መድረሳቸውን የሚገልጽ ማረጋጋጫ ከተደራጁበት ወይም ፍቃድ ካወጡበት ከፍለ ከተማ የዲዛይን ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ወር ያላለፈው ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ሞልተው ባስገቡት ሰነድ በሁሉም ገጾች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የሥራ ዝርዝር ዋጋ ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት፣ ስርዝ ድልዝ ካለ፣ በሥራ ዝርዝር በሙሉ ወይም በከፊል ሆነ በአንድ የሥራ ዝርዝር ዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ቴከኒካልና ፋይናንሽያል የጨረታ ሰነድ በተለያየ በፖስታ በማሸግ ኦርጂናልና ኮፒበማለት በፊርማ ተረጋግጦ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ጨረታ ማስከበሪያ 2% CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተመሰከረለት የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም እና የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚቸሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 23 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታውን ሰነድ በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥና ንብረት አስተዳዳር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በመምጣት በማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፍል መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ሲወስዱ በአካል ያለውን የግንባታ ሳይት ማየት ይኖርባቸዋል። ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥራ ሰዓት በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
- አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፤- ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 011 550 45664
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርትአገልግሎት ድርጅት
