የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ከዚህ በታች በአድራሻቸው የተጠቀሱትን በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶምኒየም) ላይ የሚገኙትን 3 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ለንግድ ቤት አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Kenema Pharmacy Enterprise (ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት)
ለንግድ ቤት አገልግሎት የሚውል የቤት ኪራይ ለማከራየት በድጋሚ የወጣ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ከዚህ በታች በአድራሻቸው የተጠቀሱትን በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶምኒየም) ላይ የሚገኙትን 3 ቤቶችን ማለትም፡-
- ካራ ቆሬ፡ አድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ወረዳ 03 የቤት/ቁ B/72/06 የቤቱ ስፋት 57.6 ካሬ ሜትር ኮንዶምኒየም (የጋራ መኖሪያ) ወለል (Ground) ላይ የሚገኝ፡
- ቦሌ ቡልቡላ፡ አድራሻ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር B/87/01 የቤቱ ስፋት 57.4 ካሬ ሜትር ኮንዶምኒየም (የጋራ መኖሪያ) ወለል (Ground) ላይ የሚገኝ:
- ቦሌ አያት 2፡ አድራሻ ለሚኩራ ክ/ከ/ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር B/55/03 የቤቱ ስፋት 57.76 ካሬ ሜትር ኮንዶምኒየም (የጋራ መኖሪያ) ወለል (Ground) ላይ የሚገኝ: ባሉበት ሁኔታ ለንግድ ቤት አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የጨረታ መነሻ ዋጋ፡ ለካራ ቆሬ ለአንድ ካሬ 300.00 ብር፣ ለቦሌ ቡልቡላ፡ ለአንድ ካሬ 500.00 ብር፣ ለቦሌ አያት 2፡ ለአንድ ካሬ 400.00 ብር መሆኑን እየገለጽን ማንኛውም ቤቱን በኪራይ ለንግድ አገልግሎት መጠቀምና ማዋል የሚፈልግ ተጫራች፡-
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የታደሰ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለው፣ ወይም ውል ከተዋዋለ በኋላ የንግድ ፈቃድ አውጥቶ ቤቱን በመከራየትና ለንግድ መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል (ተጫራቹ የንግድ ፍቃድ የሌለውና ጨረታውን ቢያሸንፍ አዲስ ንግድ ፈቃድ እንደሚያወጣ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት)፤
- ተጫራች የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው መሆን አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 306 መግዛት ይችላል፤
- ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያውን እና ሌሎች መረጃዎችን የያዘውን የጨረታ ሰነድ በአንድ ላይ በታሸገ ኤንቨሎፕ (አንድ ኦርጅናል እና እንድ ኮፒ) በማድረግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የግዢ ዳሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል፡፡
- ተወዳድሮ አሸናፊ የሚሆነው ግለሰብ /ድርጅት ተቋሙ በሚያከራየው ቤት ላይ የሚሰራው በህግ የተፈቀዱ ስራዎችን ብቻ ነው።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ሰሜን መዘጋጃ አካባቢ ኤስኤምኤስኤስ (SMSS) ህንጻ 3ኛ እና 4ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን፡፡
የአ/አ/ ከተማ አስተዳደር ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
