ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ለአዲአርቃይ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የግራቨል እና ሳንድ ፊልተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Tis Isat Water Works PLC (የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ለአዲአርቃይ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የግራቨል እና ሳንድ ፊልተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ ቀን |
|
1 |
01 |
የግራቨል እና ሳንድ ፊልተር |
100,000.00 |
90 ቀናት |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡
የተጫራቾች መመሪያ
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክከል ሞልተው በግልዕ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ሰኔ 25 PR 03/2017/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት።
- ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 /058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
