ወላይታ ልማት ማህበር / እ.ኤ.አ የ2025 በጀት ዓመት ዓመታዊ መጽሔት ሕትመት የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በውል ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ወልማ 05/2025
ወላይታ ልማት ማህበር / እ.ኤ.አ የ2025 በጀት ዓመት ዓመታዊ መጽሔት ሕትመት የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በውል ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች፤
- በግዥና ንብ/አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ም/ም/ወረቀት፤ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 6 /ስድስት/ ሰዓት ድረስ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ቀንና ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳጎስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ቢሮ እና በወላይታ ሶዶ ወላይታ ልማት ማህበር ዋ/ና ጽ/ቤት ከሚገኘው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማስላት 2% በባንክ የተመሰከረበት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሰራዉን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ንግድ ባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ባሉት አሥር ባሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 10% በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ማስያዝ አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ብር ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አገልግሎቱን አላቀርብም ማለት የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ልማት ማህበርግዥና ንብረት አስ/ር ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ው የሥራ ቀን እስከ 9 /ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ገቢ ሆኖ በ9፡30 ሰዓት ታሸጎ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ10፡00 ሰዓት በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ወላይታ ልማት ማኅበር ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ጨረታው ይከፈታል፤
- የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አኖረውም፡፡
ማሳሰቢያ፡- ማህበሩ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461801191/01111572842 መጠቀም ይችሳሱ፡፡
የወላይታ ልማት ማኅበር
