Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት፦

ሎት አንድ፡-የቢሮ አላቂ ዕቃዎች

ሎት ሁለት፡-የችሎት አዳራሽ ወንበሮች እና ጠረጰዛ

ሎት ሶስት፡ የሠራተኞች የደንብ ልብስ

ሎት አራት፡-ሞተር ሳይክል

ሎት አምስት -የኔትወርክ ዝርጋታ ሥራ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ሎት ስድስት፡-ማሩፍ ጎማ የፊት ለፊት እና የኋላ ለTVS ሞተር 150 CC (ሲ.ሲ.) እና RTR ሞተር 180 CC (ሲሲ)

ሎት ሰባት፡ የእስፖንጅ ፍራሽ 1 ሜትር 20 ሴንቲ ሜትር 1ኛ ደረጃ የመስኮት መጋረጃ እና የጠረጳዛ ጨርቅ

ሎት ስምንት፡-የፅዳት እቃዎች

ሎት ዘጠኝ፡ የተለያዩ የህግ መጽሐፍቶች

ሎት አስር፡-የህትመት ውጤቶች

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከላይ በሎት የተገለፁትን ዕቃዎች ለመወዳደር ወይም መጫረት የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተገለፁትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች እንደሚከተለው ይሆናል።

  1. በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
  6. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ Specification/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 / አስራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በጉራፈርዳ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለፅ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደርያ ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው ስም ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ቲክኒካል እና ፋይናሻል ዶክመንቶችን ለየብቻ በስም በታሸገ ፖስታ በማድረግ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  10. ለቀረቡት ሎት አንድ እስከ ሎት አምስት ያሉትን የጨረታ ማስከበርያ ማለትም CPO 5,000/አምስት ሺህ ብር/ እና ከሎት ስድስት እስከ ሎት አስር ያሉትን የጨረታ ማስከበርያ ማለትም C.PO 1000/አንድ ሺህ ብር/ በቲከኒካል ዶክመንት አብሮ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  11. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀኖች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኃላ ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  12. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ግዜ ለ 28 ቀን የሚቆይ ይሆናል የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  13. የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ስነ-ስርዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው:
  15. የእቃ እርክክብ የሚሆንበት ቦታ ሚዛን ከተማ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 06 59 26/ 09 33 21 51 73

 

የጉራፈርዳ ወረዳ ፍ/ቤት

Save Tender