Tender Detail

Tender Details

  • Company Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)
  • Address አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461801191
  • Websitehttps://wolaittada.org.et/
  • Deadline23 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-12-23 00:00:00
  • Categories Consultancy Service

ወላይታ ልማት ማህበር በወላይታ ዞን ምግብ ምርቶች ዋጋን ለማሻሻል አካባቢያዊ አሴት ሰንሰለቶች ላይ አጠቃላይ ጥናት ለማስደረግ የምክር አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ በውል ለመግዛት ይፈልጋል።

Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወልማ 04/2025

 

ወላይታ ልማት ማህበር በወላይታ ዞን ምግብ ምርቶች ዋጋን ለማሻሻል አካባቢያዊ አሴት ሰንሰለቶች ላይ አጠቃላይ ጥናት ለማስደረግ የምክር አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ በውል ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች ፤

      1. በግዥና ንብ/አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
      2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ም/ም/ወረቀት፤ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
      3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 6 /ስድስት/ ሰዓት ድረስ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ቀንና ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትሰን ሰፈር ቢሮ ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ቢሮ እና በወላይታ ሶዶ ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ከሚገኘው ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
      4. ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማስላት 2% በባንክ የተመሰከረበት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሰራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
      5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባሉት አሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ባሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 10% በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ብር ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል።
      6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አገልግሎቱን አላቀርብም ማለት የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል።
      7. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ልማት ማህበር ግዥና ንብረት አስ/ር ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን እስከ 9:00 ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
      8. ጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በ15ኛው የሥራ ቀን እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ገቢ ሆኖ 9:30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ በ10፡00 ሰዓት በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል። 5ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ጨረታ ይከፈታል፡፡
      9. ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አኖረውም፡፡

ማሳሰቢያ፡-ማህበሩ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 180 1191 / 011 1 157 2842 መጠቀም ይችላሉ።

ወላይታ ልማት ማህበር

Save Tender