በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
የአብክመ የኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2016 ዓ.ም
በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
- የህፃናት ማቆያ ግንባታ
- የመናኻሪያ ጥበቃ ማማ እና የመግቢያ በር ግንባታ
- የመናኻሪያ የተሳፋሪዎች ማረፊያ ግንባታ
- ስለሆነም፣
- ተጫራቾች በግንባታ ዘርፍ BC ወይም GC ደረጃ ስምንት እና ከዚያ በላይ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የምስክር ወረቀት እና እንዲሁም አንድ አመት ያልሞላው ወይም ታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለህፃናት ማረፊያ ግንባታ 25000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለመናሃሪያ የጥበቃ ማማ እና መግቢያ በር ግንባታ 35000.00 /ሰላሳ አምስት ሽህ ብር/ የመናሃሪያ የተሳፋሪዎች ማረፊያ ግንባታ 20000.00/ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብና መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 30/3/18 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እሰከ 21ኛው ቀን ማለትም 20/4/18 ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር ለእያንዳንዱ የጨረት ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻው በታሸገ ኢንቭሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ30/3/18 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ማለትም እስከ 20/4/18 ዓ.ም ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገ/ኢ/ት/መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል.።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጂቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።
በአብክመ የኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ከሚሴ አድራሻ፡
ከአዲስ አብባ ወደ ደሴ መስመር 325 KM ላይ ከሚሴ ከተማ እንገኛለን።
ስልክ ቁጥር 033 554 0364/ 033 554 0259 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ
