በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለብቸና ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ግንባታዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለብቸና ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው፡-ሎት-1፡-AM/ Bichena CIP/ CW/01–25/26 ሸድ ግንባታ የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩት ማሳደጊያ 03 Kebele near from Balwadebe river BC/GC ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ፣ሎት 3፡ AM/Bichena ClP/ CW/01/25/26 ሸድ ግንባታ የስጋ ከብት ማድለቢያ 03 Kebele near from Balwadebe river BC/GC ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ፣ ሎት-4፡- AM/Bichena ClP/ CW/01/25/26 የህፃናት ማቆያ ግንባታ Different Office buildings Children waiting house building 01 kebele BC/GC ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ፣ ሎት 2፡-AM/Bichena ClP/ CW/04/25/26 ዲች ግንባታ 04 Kebele from Nestanet Abebe house to Kasahun Merkbu house with 4 vehecle crossings and 13 pedeistrial crossings BC/GC ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ፤ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ዝርዝር መረጃውንም በጨረታ ሰነዱ ተካቷል በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
- ለሁሉም ሎቶች የታደሰ የግንባታ የምስክር ሰርተፍኬት ማቅርብ አለባቸው
- የግዥው መጠን ለግንባታ ስራ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- አንድ አመት እና ከዚያ በላይ የሆናችህ ተቋራጮች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሁሉም ለሎቶች የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል/ እና በጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑም ከአደራጃቸው መስሪያ ቤት የተደራጁበትን ዓመተ ምህረት በመጥቀስና የድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብቸና ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 መውሰድ የሚቻል መሆኑንና ለሁሉም ሎቶች ለተጠቀሱት ለእያንዳንዳቸው ግዥዎች ኦርጅናልና ኮፒን በመለየት በአንድ ፖስታ በማሸግ እስከ 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የሎት ቁጥር፤ ፊርማ፣ ማህተም፣ ስምና አድራሻ በፖስታቸው ላይ እና በሰነዱ ላይ መግለጽ አለባቸው።
- ከላይ ለተጠቀሱት ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዱ ግዥ በእንግሊዘኛ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ካለ አሸናፊው ውል ሲይዝ በአማርኛ ማስተርጐም አለበት፤ ማንኛውንም የግንባታ እቃዎችና የሰው ሃይል አሸናፊው ራሱ ችሎ የሚሰራ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ሎት፡-1 ሸድ ግንባታ ብር 75,000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት-3፡- ሸድ ግንባታ ብር 47,000.00 /አርባ ሰባት ሺህ ብር/ ሎት- 4 የህፃናት ማቆያ ግንባታ 01 ቀበሌ ብር 56,000.00 /ሀምሳ ስድስት ሺህ ብር/፣ ሎት 2፡ 04 ቀበሌ የዲች ግንባታ 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ በጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑም ከአደራጃቸው መስሪያ ቤት የተደራጁበትን ዓመተ ምህረት በመጥቀስና የድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ መግዛት ይቻላል።
- ከላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የግንባታ ስራዎች ሎት ግዥ አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት ወይም የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ለመ/ቤታችን ከተደራጁበት ቴክኒከና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት 10% የድጋፍ ዋስትና በማፃፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከመሀንዲስ ግምት አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተው ከተገኙ ለውል ማስከበሪያ 25% ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት ወይም የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ለመ/ቤታችን ከተደራጁበት ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት 25% የድጋፍ ዋስትና በማፃፍ ማቅረብ አለባቸው።
- የግንባታ ስራው /እንደስራው ባህሪ እየተለየ/ አሸናፊው ተጫራች የግል ተቋራጭ ከሆነ 15%፣ የመንግስት የልማት ድርጅት ከሆነ ደግሞ 20% የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በጥቃቅን ለተደራጁ ወጣቶች አውት ሶርስ ወይም ሰብ ኮንትራት መስጠት ይኖርበታል።
- የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫራቻ ሰነድ ላይ በነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች በቁጥር ቢያንስ ሶስትና ከዚያ በላይ ከሆነ ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበ ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች በቁጥር ከሶስት በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- በእያንዳንዱ ሎት መስሪያ ቤቱ አሸናፊነት የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘውን የተጫራቾች መመሪያ ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 1445 / 0586 65 14 46 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የብቸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
