Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር ለአባያጥር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የተለያዩ የፅህፈት/ስቴሽነሪ መሳሪያዎች፤ ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. የተለያዩ ብትን ጨርቅ የደንብ ልብስ፣ የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እና ቆዳ ጫማዎች፣ ሎት 4. የተለያዩ ህትመቶች፤ ሎት 5. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፥ ሎት 6 የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች የአባያጥር ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር ለአባያጥር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እገልግሎት የሚውሉ

ሎት1. የተለያዩ የፅህፈት/ስቴሽነሪ መሳሪያዎች፤ ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. የተለያዩ ብትን ጨርቅ የደንብ ልብስ፣ የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እና ቆዳ ጫማዎች፣ ሎት 4. የተለያዩ ህትመቶች፤ ሎት 5. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፥ ሎት 6 የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች የአባያጥር ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያስታውቃል፡፡

L የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ የጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. የዕቃውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 (መቶ ሃምሳ ) ብር ብቻ በመከፈል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 20 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 1 % በባንክበተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአባያጥር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 21 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ28/3/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 13/04/2018 ዓ.ም ባሉት 15 አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከምሽቱ 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው።

11. የጨረታ መዝጊያውንና መከፈቻውን ከመንግስት ስራ ውጭ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ ቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡

12 ተወዳዳሪ ድርጅቱ ያሸነፈበትን ዕቃዎች በአባያጥር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ከፍል ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ሃላፊነት አለባቸው፡፡

13. ውድድሩ በጥቅል/ በሎት ስለሆነ ተጫራቾች በከፈል መሙላት አይችሉመ፡፡

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ/ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ሲፈልጉ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0949117957 / 0961177892 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ-ጨረታውን ስትሞሉ በጥቅል ዋጋ መሆኑን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡

የድምር ስህተት ስርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ነው፡፡ ስትሞሉ ጥንቃቄ በተሞላ መሆን አለበት፡፡

አድራሻ፡- አባያጥር ጤና ጣቢያ ከሸዋሮቢት ከተማ 28 ኪ.ሚጋባ ብሎ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት

Save Tender