Tender Detail

Tender Details


በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 2ኛ ዙር

ቁጥር 002

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች እና ሌሎች

ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 3. የደንብ ልብሶችና የጽዳት እቃዎች

ሎት 4. የህትመት ውጤት

ሎት 5. የጉልበት አገልግሎት

ሎት 6. ቋሚና አላቂ እቃዎች

በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደርፋይናንስ ጽ/ቤት ካራ ቆሬ የሚገኘው ህንፃ ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡

ተጫራቾች ማሟላት የሚኖርባቸው: -

* የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ የአስገቡት ዋጋ ለሁሉም ሎት 1.5 % በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ሲፒአ ማስያዝ አይጠበቅባቸውም በምትኩ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው የሚቀርበው ደብዳቤ በኃላፊ የተፈረመ መሆን አለበት፡፡

የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ለቫት ተጠቃሚዎች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡

ከጉልበት ተጫራች ውጭ ማንኛውም ተጫራች የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ኮፒና ዋና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አሸናፊ ተጫራች በሰነድ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው፡፡

የእቃ ማስረከቢያ ቦታ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል ለአንድ እቃ ሁለት አይነት ናሙና ያቀረበ ከውድድርውጭ ይሆናል፡፡

ለጉልበት አገልግሎት ተወዳዳሪዎች ከመንግስት አካል የተደራጁበትን ማስረጃ ማቅረብ ብቻ በቂ ነው፡፡

ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል፡፡

አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

አሸናፊ ድርጅት ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በıo (አስር) ቀን ውስጥ እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡

የጨረታው ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከአስር የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች (በጨረታው) የተሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ጽ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 011 8 330804 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ ካራ ቆሬ ሩታ ከግራር 200 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በኮለፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender