ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ ስራ የሚያገለግል Fargo color Ribbo A FARGO Certified CR-80 Ultra card III ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥርማዕ/ ኢት/ ትራ/መን/ /ል/ ቢሮ መደ 003/2018
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ ስራ የሚያገለግል Fargo color Ribbo A FARGO Certified CR-80 Ultra card III ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች: -
1, የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው::
3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ፡፡
4. የቲን ተመዝጋቢነት ምስከር ወረቀት ያለው፡፡
5. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ንብ/አስ/ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6. በአንላይን የተመዘገበ
7. የዕቃውን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኢንቬሎፕ የቴከኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒከና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኢንቬሎፑ የውጭገጽ ዋና ኦርጂናል ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና CV ኮፒ ተበሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ በዋናው (ኦሪጅናል/ ሆኖ ኮፒ ኤንቬሎፕ ውስጥ ከፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፡፡
10. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር የሚውል ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡0ዐ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡3ዐ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ላይ በተጫራች ፊት ተከፍቶ በንባብ ይሰማል ፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ማንኛውም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌድሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ቼከ ወይም ከታወቀ በባንከ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
12 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ /አቅራቢ/ዎች /ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0991415433 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
13. ቢሮ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የቢሮ አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥዕት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
