Tender Detail

Tender Details

  • Company Global Insurance Company S.C (ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-156-58-51
  • Websitehttps://www.globalinsurancesc.com/
  • Deadline13 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለተሸከርካሪዎች ከብር 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) እንዲሁም ለተሽከርካሪ ቅሪት እና ሌሎች ቅሪት አካላት ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-13 00:00:00
  • Categories Vehicle , Vehicle Spare Parts

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Global Insurance Company S.C (ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)


 

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን እና የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት ለመግዛት የሚፈልጉ ሱማሌ ተራ (ጎበና አባጥጉ መንገድ) ከሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሲ.አር.ቢ.ሲ በስተቀኝ ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ በግምት መቶ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያችን የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery) ውስጥ በማየት እስከ ታህሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጫረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይችላሉ::

  • ተጫራቾች ቅሪት ንብረቾችን እና ተሽከርካሪዎችን ከ እሁድ ህዳር 28 ቀን 2018 ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ እስከ ታህሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  • ጨረታው ታህሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 3:30 ሰዓት ተዘግቶ በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ላይ ይከፈታል።
  • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ወይም (Global Insurance Company S.C) ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸከርካሪዎች ከብር 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) እንዲሁም ለተሽከርካሪ ቅሪት እና ሌሎች ቅሪት አካላት ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም።
  • ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሸከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፈናል። በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉት ማናቸውም ወጪዎች በገዢው ሙሉ በሙሉ ይሸፈናል።
  • ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
  • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
  • አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች እቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጭ ሳይነጣጥሉ በአንድ ጊዜ ከፍለዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ አሸናፊዎች የስም ዝውውር እስከ ስድስት ወር ድረስ ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ጉዳይ ኩባንያው ኃላፊነት አይወስድም።
  • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ :- 011-156-58-51 / 011-126-33-85/68

/011-158-05-77

ፋክስ:- 011-156-23-34

 

Save Tender