የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የተለያዩ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian medical Association (EMA) (የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር)
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር
በድጋሚ የወጣ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የተለያዩ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ማንኛውም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝሮች በማሟላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት አራት ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ጀርባ ወይም ከአራዳ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮችን በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን መውሰድና መወዳደር ይችላሉ።
- TIN፣ VAT፣ ምዝገባ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው
- የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ቢሮችን በመቅረብ የጫረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- እነዚህ እቃዎቹ የሚገኙት የተለያዩ ሁለት ቦታ በሚገኝ እስቶራችን በመሆኑ አሸናፊ ተጫራችም እቃዎቹን ሲረከብ ከነዚህ ከሁለት ቦታ እንደሆነ ማወቅ ይኖርበታል።
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ5 /አምስት/ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ እቃውን መረከብ ይኖርበታል፤ ይህንን መፈፀም ባይችል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስለት ሲሆን ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን መግዣ በነጠላ ወይም በጥቅል ዋጋ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን የሚቀርበው ዋጋ ተ.እ.ታን የሚያካትት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በመሙላት ከታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧት 2፡30-6፡30 እንዲሁም እስከ ታህሳስ 10,2018 ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ታህሳስ.10, 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ተዘግቶ ታህሳስ,11, 2018 ዕለት ከቀነ 3፡30 የጨረታ ኮሚቴውና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መሥሪያ ቤት የድርጅቱ መሰብሰቢያ ቦታ ይከፈታል።
- ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችን ለማየት የሚፈልግ ተጫራቾች ታህሳስ 4,2018 ከቀነ 4፡00 ሰዓት ማየት ይችላል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮጵያ ህክምና ማህበር
011-1-25-01-66 መጠየቅ ይችላሉ
አዲስ አበባ
