Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን/ኮምቦልቻ/
  • Address , Phone: 0335514657
  • Website
  • Deadline21 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-21 00:00:00
  • Categories Materials , Construction Materials And Raw Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በዩኒሴፍ በጀት ሎት 1 የግንባታ ማቴሪያሎች፣ ሎት 2 የአካባቢ ማቴሪያሎች አሸዋና ጠጠር/ እንዲሁም በመደበኛ በጀት ሎት 3 የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ሎት 4 ልዩ ልዩ የሚወገዱ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በዩኒሴፍ በጀት ሎት 1 የግንባታ ማቴሪያሎች፣ ሎት 2 የአካባቢ ማቴሪያሎች አሸዋና ጠጠር/ እንዲሁም በመደበኛ በጀት ሎት 3 የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ሎት 4 ልዩ ልዩ የሚወገዱ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. የጨረታ መለያ ቁጥር ቃ/ወ/ግ/ጨ/003/2018
  2. ተጫራቾች ሕጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መረጃ ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ሲኖርበት የግዥው መጠን ከብር 200.000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. የሚፈለገውን እቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ። ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ  15 ቀናት 11፡00 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።
  5. ተጫራቾች ለሎት 1 - 80,000 /ሰማንያ ሺህ ብር/ ለሎት-2. 40.000/ አርባ ሺህ/ ብር ፣ ለሎት-3 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር ለሎት -4- 10,000 /አስር ሺ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም።
  6. የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ  ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ፖስታውን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ ዕለት 4:00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መከፈት ኢያግደውም።
  8. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ወይም እሁድና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
  10. ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሎት ድምር ነው።
  11. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
  12. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም።
  14. አሸናፊው ተወዳዳሪ ኦርጂናል እቃዎችን ማቅረቡ እንደተጠበቀ ሆኖ በሎት 2 የተገለፀውን ማለትም የአካባቢ ማቴሪያል በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፁት ቀበሌዎች ለሥራው በሚያስፈልገው መጠን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335514657 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን/ኮምቦልቻ/

Save Tender