በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት የታካሚ ለይቶ ማቆያ ክፍልን ለማደስና ለማሻሻል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 1.2/18
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት የታካሚ ለይቶ ማቆያ ክፍልን ለማደስና ለማሻሻል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በሥራ ተቋራጭ ዝርዝር የተመዘገቡና ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ህጋዊ እውቅና ካለው ባንክ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በ10 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ፣ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት ለየብቻው በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን የአንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10 የሥራ ቀናት የተዘጋጀውን ሰነድ ከየካ ከ/ከተማ ወረዳ 08 / ጨፌ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ የረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 413 ቀርበው በየሎቱ 100.00 /አንድ መቶ ብር ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ መጫረት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት ዋጋ /10,000.00/ /አስር ሺህ ብር/ የሕክምና ሪኤጀንት አላቂና ቋሚ እቃ ሎት 1 በጨፌ ጤና ጣቢያ ስም ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ /CPO/ ብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከገበት ጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ጨረታውም ማስታወቂያው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ሕዝባዊ ሃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አከፋፈት ስርዓት ላይ በራሳቸው ፍቃድ ባይገኙ ጨረታው አይስተጓጎልም።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ ሱመያ መስጊድ ጀርባ ከማጂክ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0116663281 ወይም 0916-51 87-02
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ የግዥ ቡድን መሪ
