የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የዕቃዎች አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 08/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Water Works Construction Enterprise (WWCE) (የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB WWC 08/2018
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የዕቃዎች አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 08/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ. ቁ |
የሎት ቁጥር |
ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goods
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
|
1 |
ሎት-1 |
Generator and with all accessories |
set |
ጥቅል |
|
2
|
ሎት-2
|
Sub lot-1 submersible pump with all accessories |
set |
ጥቅል |
|
Sub lot-2 H.surface pump with all accessories |
set |
ጥቅል |
||
|
3
|
ሎት-3
|
Sub lot-1 Electrical materials |
Pcs/ set |
ጥቅል |
|
Sub lot-2 Common Main Distribution Board For Pump & Generator House |
|
|
||
|
4 |
ሎት-4 |
Surge tank=v=10001 |
set |
ጥቅል |
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/፤የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት 1 ብር 165,000.00 [አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር] ፤ ለሎት-2 ብር 300,000.00 [ሶስት መቶ ሺህ ብር] ፤ ለሎት-3 ብር 100,000.00 [አንድ መቶ ሺህ ብር] እና ለሎት-4 ብር 100,000.00 [አንድ መቶ ሺህ ብር] በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በውሀ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከድርጅቱ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴከኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 20 ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- 6.የማቅረቢያ ቦታ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኮረፖሬሽኑ ስቶር/መጋዘን ድረስ አሸናፊው ማቅረብ ይኖርበታል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቀጥር- 058-222-14-79 መጠየቅ ይቻላሉ።
ማሳሰቢያ፤- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መገዛት ብቻ እንጅ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃስን።
አድራሻ:-
ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት
ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ፖ.ሣ.ቁ 106
ስልክ ቁጥር 058222-1479
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
