ድርጅታችን ኬ.ኤ.ኤም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጨረታ ቁጥር 009/2018 በድርጅቱ ዱከም በሚገኘው የፒቪሲ ኮርኒስ ፋብሪካ መጋዘን ውስጥ የሚገኙ ለፒቪሲ ኮርኒስ ምርት የሚያገለግሉ ኦሪጂናል ጥሬ እቃዎችን እና በድጋሚ የተመረቱ ጥሬ እቃዎችን /Recycled PVC raw materials/ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ኬ ኤ ኤም ኃ/ የተ /የግል ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 009/2018
ድርጅታችን ኬ.ኤ.ኤም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጨረታ ቁጥር 009/2018 በድርጅቱ ዱከም በሚገኘው የፒቪሲ ኮርኒስ ፋብሪካ መጋዘን ውስጥ የሚገኙ ለፒቪሲ ኮርኒስ ምርት የሚያገለግሉ ኦሪጂናል ጥሬ እቃዎችን እና በድጋሚ የተመረቱ ጥሬ እቃዎችን /Recycled PVC raw materials/ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ስለ አጠቃላይ የጨረታ ሁኔታ ይረዱ ዘንድ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደንቦችን፣ ከጠቅላላ ማብራሪያና አፈጻጸም ሂደቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሲሆን ተወዳዳሪዎች የጨረታ መስፈርቱ የሚጠይቀውን መወዳደሪያ ነጥቦች በማሟላት ፋይናንሻል ፕሮፖዛል (ዋጋ ማቅረቢያችሁን) እንድታቀርቡ እያሳወቅን፤ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ማስከሪያ /Bid Bond/ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ አዲስ አበባ ን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 በጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ህንፃ ወለል/GROUND FLOOR/ ላይ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 3 ቀን,2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የዕቃዎችን ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
- ጨረታው ታህሳስ 3 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
- በጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል (የዋጋ ማቅረቢያ) ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ /cpo/ በአንድ ላይ በማድረግ አንዲሁም በጥንቃቄ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 በጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ውስጥ ነው።
- ዝርዝር የጨረታ መመሪያው ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለባቸው።
- የዕቃዎቹን ናሙና ለመመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና መታወቂያውን /ውክልና/ በመያዝ ን/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክግቢ ውስጥ መመልከት ይችላል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተከበረ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር
0911523393/ 0910158570 ይደውሉ
ኬ ኤ ኤም ኃ/ የተ /የግል ማህበር
