የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን የኔትወርክ ዝርጋታ ዕቃዎች፤ የጨርቃ-ጨርቅ እና የሌሊት አልባሳት፣ የሞተር ዕቃዎች መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን የኔትወርክ ዝርጋታ ዕቃዎች፤ የጨርቃ-ጨርቅ እና የሌሊት አልባሳት፣ የሞተር ዕቃዎች መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. በግብር ከፋይነት ተመዘግበው የአቅራቢነት ሠርትፈኬት ኖሯቸው የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝገቢ ሆነው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ እንዲሁም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 100.00 በመከፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ንብ⁄ አስ/ ዳይ/ ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ _ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሽገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመረያ ጋር አባር ተድርጎ ተያይዟል።
3. ይህ ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ልከ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻ በግልጽ በመሙላት በማህተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
5.ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፈነቱ የተጫራቾች ይሆናል፡፡
6. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
- ሀዋሳ ወደ ሪፈራል በሚወሰደው መንገድ ላይ ከሂል -ሳይድ ሆቴል በስተጀርባ
- መሥሪያ ቤቱ ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፌልግዎ በዚህ ስልክቁጥር ይደውሉ 0462121134 ወይም 0462121140 መደወል ይችላሉ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
