የአንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥራ/ማ በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሃና ፉሪ 5.81 ሳይት 2B+G+13+ፐ የጋራ ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመጀመሪያውን ፌዝ (phase 1) ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
የአንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥራ/ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መስያ ቁጥር ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2018
የአንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥራ/ማ በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሃና ፉሪ 5.81 ሳይት 2B+G+13+ፐ የጋራ ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመጀመሪያውን ፌዝ (phase 1) ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ኮንትራክተሮች፡-
1, በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2, የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
3, የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
4. በኮንስትራክሽን ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ያላቸው፤
5, በማንኛውም መስሪያ ቤቶች ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ እና በመንግስት የኮንስትራክሽን ስራ የግልፅ ጨረታ አፈፃፀም መመሪያ መስፈርት መሠረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ BC-2 /GC-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑና ሦስት ዓመት ተከታታይየሠሩትን የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በየትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይኘሮጀከቶች ህጋዊ ውል ገብተው ያለስራ ጥራት ጉድለት ያጠናቀቁ፣
- ከ2013 ዓ/ም ጀምረው ባለው ጊዜ ውስጥ በተመሳሳይ ስራ: አሸንፈው ያጠናቀቁትን ኘሮጀክቶች በዝርዝር ከነመልካም ስራ አፈፃፀም ሰርተፍኬታቸው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን /ቴክኒክ/ ብቃት መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦርጅናል) ኮፒ ሲጠየቁ አቅርቦ ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተመሳከሮ ትከክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውንም ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲሞሉ ኪ.ተ.እ.ታ በፊት ያለ የነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ቴክኒካል ውድድሩን ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሽያል ሠነድ አይከፈትም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ unconditional Bank Guarantee ወይም የክፍያ ማዘዣ CPO 500,000.00 በእንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማ ለ90 ቀናት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማና ማህተም ያለበት ሰነድ መግባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ካሟሉ በኋላ የግንባታ መሣሪያዎቻቸውን በቦታው አጓጉዘው ማድረስ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማጭበርበር፣ ሙስና እና ማታለልን በተመለከተ ላለመፈፀም በኢትዮጵያ ሕጐች የተደነገገውን የሚያከብር እና የሚያስከብር መሆን አለበት
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት በኋላ ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፉበት ዋጋ 10% un conditional Bank Guarantee ወይም (CPO) አሰርተው ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ በጨረታ ሰነዱ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል፣ ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ማስረጃ (ዋጋ ላይ) ስርዝ ድልዝ (ፍሉድ) ካለበት ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- ለጨረታ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት የማይቀየር (የፀና) ይሆናል፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ቀን፡-
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ የማይመለስ 2000.00 ብር በ 2mer.cc/andinet15 ሊንክ በመጠቀም ከፍያ በቴሌ ተፈፅሞ ሲቀርብ ለዚሁ ጨረታ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሶፍት ኮፒ ከ 2መርካቶ ዶ.ኮም መውሰድ ይችላሉ ወይም በአንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማ በተከፈተ የንግድ ባንከ ሂሳብ 1000554782427 ወይም በ+2519-11-43-37-00 በቴሌ ብር (በጸሎት የማነ) በመከፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ፣ ሲቀርብ ለዚሁ ጨረታ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ኃይሌ ጋርመንት አዲሱ አትክልት ተራ ፊትለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው በአንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሰ/ማ ቢሮ ከሠኞ እስከ ቅዳሜ 3፡30 - 10:30 በመገኘት ሀርድ ኮፒ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው ታህሳስ 9/2018 ዓ/ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሃይሌ ጋርመንት አዲሱ አትከልት ተራ ፊትለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው በአንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ: +2519-11-36-55-99/+2519-11-91-32-03/+2519-11-43-37-00/+2519-11-
89-07-59 አዲስ አበባ፣
አንድነት 15 የጋራ መኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማ
