Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0961178110
  • Website
  • Deadline22 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price2000.00
  • Bid Security500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-22 00:00:00
  • Categories Construction Works

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው መንግስትና በህዝብ ተሳትፎ አዳራሽ ከነ-ወንበር ገጠማ፣ ዘመናዊ የጉራጌ ባህላዊ ጎጆ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤት፣ የአዳራሹ አጥር እና የጥበቃ ቤት ጨምሮ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/መ/ቁ/04/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው መንግስትና በህዝብ ተሳትፎ አዳራሽ ከነ-ወንበር ገጠማ፣ ዘመናዊ የጉራጌ ባህላዊ ጎጆ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤት፣ የአዳራሹ አጥር እና የጥበቃ ቤት ጨምሮ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡-

  1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ።
  3. ተቋራጭ በግንባታ ስራ ተቋራጭ በደረጃ BC-3/GC-3 እና ከዛ በላይ የሆኑና የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸው የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተቋራጮች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫ የ2018 የታደሰ የበጀት ዓመቱ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባቸው።
  6. ተቋራጮች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት በኦን ላይን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ሰርተፊኬት e-GP /Electeronic Governmente Procuremente ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  7. የ2018 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2018 E.C)
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተቋራጮች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡
  9. ተቋራጮች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ የተጠየቀውን መረጃ ብቻ በአግባቡ የሚያቀርቡ እና ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፤ ስርዝ ቢፈጠር በተፈጠረው ቦታ ፊርማ የማኖር ግዴታ መሆኑን መረዳት ይጠበቃል፡፡
  10. ተቋራጮች የጨረታው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመት ሲያቀርቡ፡-

ሀ. ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡

ለ. ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊከ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ በድርጅቱ ባለስልጣን በእያንዳንዱ ገጽ የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት ሆኖ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት እሰከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

  1. ተቋራጮች የግንባታ ስራው የሚሰራበት ቦታ በአካል በማየት ስለ ማየታቸው ከጌታ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት የተወከለ አካል የተፈረመበት እና ማተም የተደረገበት መረጃ በመቀበል ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል፡፡
  2. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተቋራጮቹ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሽያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  3. ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለ148 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡
  4. ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው የግንባታ ስራዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል፡፡
  5. ተቋራጮች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረተው ከመክፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት፡፡
  6. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተቋራጮች በግንባታ የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በተከታታይ እስከ 21ኛው ቀን 2፡30 ድረስ የጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ማይመለስ ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ 21 /ሃያ አንደኛ/ ቀን የህዝብ-በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰዓት በጨረታ ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8፡30 ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

  1. ግዢ ፈጻሚው አካል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም (በከፈል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  2. በአፈጻጸም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለቴክኒካል ዶክመንት የተጠየቀውን መረጃ ብቻ ግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  4. የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ ከሚቆጣጠራቸው ፕሮጀክቶች ከሁለት በላይ ያላቸው መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  6. ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ ቫትን ባካተተ ሁኔታ መሙላት ይጠበቅባችኋል ካልሆነ ቫት እንደ ተካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ:- ስልክ ቁጥር/0961178110/0967441304/0925838193 መደወል ይችላሉ፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት

 

Save Tender