የማ/ኢ/ከ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሁለት ሎት ማለትም የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ (ሎት:- 01) እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ (ሎት-02) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕ/ኢ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት (ሀላባ ቁሊቶ)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
የማ/ኢ/ከ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሁለት ሎት ማለትም የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ (ሎት:- 01) እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ (ሎት-02) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት-
በሎት-01 የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ (ለሁስተኛ ጊዜ የወጣ) እና
በሎት-02 የኢሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ
1. የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ እና የታደሰውን ንግድ ፈቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ላይ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይየሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
3. በኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤
4. በተሽከርካሪዎች ጥገና ላይ ለምትወዳደሩ ጋራዦች (ተጫራቾች) ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤
5. ተጫራቾች ለሎትı ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለሎት 2 ብር 36,400.00 (ሰላሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ ከሆነ የሚያሲዙት ከ9o ቀን ያላነሰ ጊዜ ያለው ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
6. የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱን ሎት በመከፈል ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 22 በመግዛት ለሁለቱም ሎቶች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎችን በየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. መጀመሪያ ዙር የሁለቱም ሎቶች ቴክኒካል ዶክመንት የሚከፈት ሲሆን በቴክኒክግምገማው ዝቅተኛ መስፈርት ካላመጡ ለፋይናንሻል ውድድር የማያልፉ መሆኑንና ፋይናንሻል ሰነዳቸው የማይከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
8. ለተሽከርካዎች ጥገና ጋራዥ የቴከኒከ ግምገማው ከ50% እና ፋይናንሻል 50% የሚያዝ ሲሆን በቴክኒከ ግምገማው ከ 100% ከ70% በታች ወይም ከ50% ከ35% በታች የሚያመጡ ተወዳዳሪዎች የዋጋ ሰነዳቸው የማይከፈት መሆኑን ጭምር እንገልፃለን፣
9. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ከ60 ቀን ማነስ የለበትም።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
11. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
12. ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጥር 046-5561645 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የማዕ/ኢ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት (ሀላባ ቁሊቶ)
