Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት
  • Address ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline18 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-12-18 00:00:00
  • Categories Construction Works

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 04,06, እና 07 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 04,06, እና 07 07 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሸነሪዎች በ በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከጥሎትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

ተ.ቁ

የፕሮጀክት ስም

ወረዳ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

አድራሻ

ተቋራጭ

1

ሰብ ቤዝ እና ድሬኔጅ ብሎክ 45

06

2%

ደረጃ 7 እና 8 ብቻ ተቋራ

90 ቀን

ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ

2

ሰብ ቤዝ እና ድሬኔጅ ብሎክ ዐ8፤ እና ድሬኔጅ ስራ ብሎክ 13

07

ደረጃ 7 እና 8 ብቻ ተቋራ

90 ቀን

3

ሰብ ቤዝ ብሎክ

04

2%

ደረጃ 7 እና 8 ብቻ ተቋራ

90 ቀን

ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ

4

ሰብ ቤዝ ብሎክ 56

03

2%

ደረጃ 7 እና 8 ብቻ ተቋራ

90 ቀን

ደረጃ 7 እና 8 ብቻ ተቋራ

1. ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የ2017 ዓ.ም የከፈሉ፤ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የበቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስከር ጣረቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ አርጂናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፈርማ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀከት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (MD BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸክ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል። በተጨማሪም የታሸገውን 2 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፈርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።

3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት (Work Days) ቅዳሜን ጨምሮ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ ፈማ/ጽ/ቤት መሰረት ልማት በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የዘዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን (work Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎፈ/ማ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።ማላሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 16 ኛው የሰራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

4. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break Down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመmmy (unbalanced rate) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል።

5. ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት።

6. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

7. እጃቸው ላይ ምንም አይነት ስራ እንደሌላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ስራም ካላቸው 75% መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።

8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ:-

የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/ጎ/ፌ/ማ/ጽ/ቤት መሰረተ ልማት ቡድን በጹሑፍ ጥያቄ መቅረብ ይችላሉ፡፡

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት

Save Tender