Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline01 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityአምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር)
  • opening date2026-01-01 00:00:00
  • Categories Construction Works , Contractors

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የክልል ኤርፖርቶች፡- አሶሳ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ጎንደር፣ ጎሬ መቱ፣ ሐዋሳ፣ ሁመራ፣ ሚዛን አማን፣ ነገሌ ቦረና፣ ሽሬ እና ያቤሎ ኤርፖርቶች የአጥር ግንባታ ደረጃ-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላና የህንጻ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T591

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የክልል ኤርፖርቶች፡- አሶሳ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ጎንደር፣ ጎሬ መቱ፣ ሐዋሳ፣ ሁመራ፣ ሚዛን አማን፣ ነገሌ ቦረና፣ ሽሬ እና ያቤሎ ኤርፖርቶች የአጥር ግንባታ ደረጃ-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላና የህንጻ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ በአገር ውስጥ የተመዘገቡና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግስት ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T591 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ፣ የጨረታ ቁጥር፡ የድርጅቱን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ 180 ተከታታይ ቀናት ነው፡፡

ተጫራቾች አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)፣ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ መሆን ይኖርበታል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ውድቅ ይሆናሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

በስልክ ቁጥር: +251-115-17 89 18

ኢ-ሜይል: EskedarG@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

Save Tender