Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0334490061
  • Website
  • Deadline16 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security1%
  • opening date2025-12-16 00:00:00
  • Categories Building Materials , Cloth And Shoes

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለወረዳው ሴከተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድብ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/03/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለወረዳው ሴከተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድብ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ሎት 1፡ የደምብ ልብስ ግዥ፣

ሎት 2 የውሃ ዕቃዎችና የግንባታ ዕቃዎች ግዥ፣

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተሟላ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሀሳብ መስጫ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ' ማድረግ አይቻልም።

6, ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት የሚወጣ ጨረታ እንዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

9. ተጫራቶች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመቀበያ ደረሰኝ በእ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በምርጫቸው በእንዱ ከዋና /orginal/ የመወዳደርያ ሰነዳቸው ጋር ማቅርብ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ /ማቅረብ አለባቸው።

11.ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 22/ 03/2018 ዓ.ም እስከ 6 /04/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16 ኛው ቀን ማለትም 07/04/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል።

12.ጨረታው ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በዚሁ ቀን ማለትም በ 07/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 በአ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የስራ ቀን ውጭከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

13.ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሠዓት የንግድ ፍቃድና ሁሉንም ማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናሉንና የማይመለስ አንድ አንድ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት አለባቸው፡፡

14.መ/ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በሎትም ሆነ በተናጠል አማራጩን ይዞ በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ብቻ ሲሆን ከሚፈለጉት እቃዎች መካከል ለከፊሎቹ ብቻ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል።

15.መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0334490061 ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን

የአርጡማ ፋርሲ ወረ-ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender