Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301548
  • Website
  • Deadline16 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security40,000.00
  • opening date2025-12-16 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ካፒታል ፕሮጀከቶችን ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው ተወዳዳሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መስያ ቁጥር-004/2018

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ካፒታል ፕሮጀከቶችን ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው ተወዳዳሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 ከጉብሬ ዶሮ እርባታ እስከ አፓርትመንት ጀርባ(ዲችና ጠጠር መንገድ ጥገና ገረጋንቲ)

ሎት-2 ከአሊ ቤት እስከ ወልቂጤ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ኮብል

ሎት-3 ከማራኪ ካፌ እስከ ከተማ ፖሊስ ኮብል ጥገና

ሎች 4 ከአዲስ ህይወት ት/ቤት እስከ ማህበር ቤት (ጠጠር መንገድ ጥገና ገረጋንቲ)

በዚህም መሰረት-

ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብርየከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች በፌዴራል መንግስት የግዥ ስርዓት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና eGP ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ CPO ለእያንዳንዱ ሎት 40,000ብር በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ማለትም የሚፈልጉትን ጨረታ አይነት (ሎት) የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ስራ/ሂደት ከፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ተወዳዳሪዎች ከአደራጅ መ/ቤታቸው ሁሉንም የማህበሩ አባላት LMIS ምዝገባ ማድረጋቸው የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ

1ኛ/ማንኛውም ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ከዋጋ ጥናት መረጃ ጋር 15% ከፍ የሚል ከሆነ ውድቅ ይደረጋል።

2ኛ/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል።

3ኛ/ ከዋጋ ጥናቱ ከ15% በታች በሆነ ዋጋ ጨረታ የሚያሸንፍ ተወዳዳሪ ያለቅድመ ከፍያ ስራ ይጀምራል። እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 20% የሚያሲይዝ መሆኑን እንገልፃለን።በተጨማሪም ማስያዣ (ሪቴንሽን) 7% መሆኑን እንገልፃለን።

4ኛ/ በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ (Arithmetic Error) የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መከፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡

5ኛ/ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

6ኛ/መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

➢ ለበለጠ መረጃ አድራሻ፦ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ ገኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113301548/0911921780/ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender