ድርጅታችን ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር የዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ሮለር እና የግሬደር የተለያዩ አዲስ ኦርጅናል መለዋወጫዎች ቅድመ ሁኔታውን ለሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር
የኮንስትራክሽን ማሽኖች መለዋወጫ
ሽያጭ ጨረታ
ድርጅታችን ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር የዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ሮለር እና የግሬደር የተለያዩ አዲስ ኦርጅናል መለዋወጫዎች ቅድመ ሁኔታውን ለሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከሕዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ከድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት እና የመለዋወጫዎቹን ሳምፕል ማየት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን::
በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች
- ንግድ ምዝገባ፣
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ማስረጃ፣
- በውክልና ከሆነ ውክልና እና መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ተብሎ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ታህሳስ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
አሸናፊው ተጫራች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ገንዘብን ሙሉ በመሉ በመክፈል ንብረቱን መውሰድ ይኖርበታል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0983 93 29 95/0930 07 71 80
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኤን.ኤፍ.ኤ ቢዝነስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር
