Tender Detail

Tender Details

  • Company በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የአጉቤሳ ቀበሌ ሂላል መስጊድ
  • Address በአሶሳ ዞን ፡ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910 00 03 29
  • Website
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በአጉቤላ መስጂድ ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት አጉቤላ ወጣት ባለሀብቶች የመስጂዱን ግንባታዎች በግልጽ ጨረታ በማሳወጅ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የአጉቤሳ ቀበሌ ሂላል መስጊድ


 

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአጉቤላ መስጂድ ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት አጉቤላ ወጣት ባለሀብቶች የመስጂዱን ግንባታዎች በግልጽ ጨረታ በማሳወጅ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት

በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በመስጅድ ግንባታ ልምድ ያላቸው ሲሆኑ ለጨረታዉ ውድድር ማቅረብ ያለባቸው መስፈርቶች በአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለስልጣን፤ ከክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የተመዘገቡ የብቃት ማረጋገጫቸውን ያሳደሱ

1.     የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር እና የአቅራቢነት ሰርተፍኬት እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የ2016 በጀት ዓመት ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ በኦዲተር የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሟልተው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው። መልካም ሥራ አፈፃፀም ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ፕሮጀክት በውል ተረከበው በውሉ መሠረት ሠርቶ በጊዜያዊ ወይም ለመጨረሻ ያስረከቡበት የርክክብ ቬርቫል የፕሮጀክቱ ብር ተደምሮ ከ4,000,000 ብር በላይ የያዘ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋጋጠ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንት ወይም CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በግዥ መመሪያ ላይ ከተፈቀዱ ዘዴዎች በአንዱ አዘጋጅተው ማቅረብ አለባቸው።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።

3.     ሁሉም ተጫራቾች የግንባታ ማቴሪያሎችን በራሳቸው ወጪ አጓጉዞ ወደሳይት አስገብተው የሚገነቡ መሆኑን በግልጽ የተረዱ መሆን አለባቸው።

4.     ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የሥራ ሳይቱን ሆነ ሥራውን በራሱ ወጪ ተንቀሳቅሰው ስለሥራው ይዘትና ሳይት በማየት ሁኔታውን ካረጋገጠ በኋላ ነጠላ ዋጋ መሙላት አለበት። ስለማየቱም ፕሮጀክቱ ከሚሰራበት ከቀበሌው አስተዳደር መረጃ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።

5.     ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ግንባታ ሥራ ወስደው አጠናቀው ያስረከቡበት መልካም ሥራ አፈፃፀም እና ጊዜያዊ ወይም የመጨረሻ ርክክብ ያደረጉበት ሰርተፍኬት ቢያንስ አንድ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ለሎት-1

6.     ተጫራቾች የፋይናንሻል ጨረታ ሰነድ ሞልተው በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም በማድረግ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ኮፒ-1 እና ኮፒ - 2 እንዲሁም ኦርጅናል ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት የጨረታው ዓይነት ከተጻፈ በኋላ በእናት ፖስታ አጠቃሎ በማሸግ በእናት ፖስታው ላይ በተመሳሳይ ማህተምና ስልክ የጨረታውን ዓይነት በመጻፍ እንዲሁም የቴክኒካል ሰነዶች አንድ አርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻው ከታሸገ በኋላ ኮፒ፤ ኦርጅናል ተብሎ በፖስታዎች ላይ ከተገለጸና ማህተም ከተመታ የጨረታው ዓይነት ተገልጾ በተመሳሳይ በእናት ፖስታ ተጠቃሎ በማሸግ በፖስታው ላይ ማህተምና የጨረታ ዓይነት ተገልጾ በዕለቱ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መግባት አለበት:: የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ መካተት አለበት:: በሌላ በኩል የአርቲሜቲክ ስህተት ካስነበበው ዋጋ ከ3% በላይ እንዲሁም ያቀረበዉ ዋጋ ከመሃንዲስ ግምት ከ15% በላይና ከ25 በታች ያቀረበ ቅናሽ 10% በላይ ሲሆን ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

7.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሲቀር በሚቀጥለው ሥራ ቀን ሂደቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል።

8.     መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.     ተጨማሪ መረጃ ለማገኘት በስልክ ቁጥር 0910 00 03 29/0913 83 65 08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የአጉቤሳ ቀበሌ ሂላል መስጊድ

Save Tender