ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት 11-10B ስራ ግንባታ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/MOND/1522/18
ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት 11-10B ስራ ግንባታ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፤
|
ተ.ቁ |
የስራ ዝርዝር |
መጠን |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
የFountain Pump and Nozzle አቅርቦት እና ገጠማ ስራ |
በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠቀው መሠረት |
09/04/2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 |
09/04/2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡15 |
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት በጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ለሚገነባው ሳይት የሚያቀርቡበት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ ጨረታው እስከሚዘጋ ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ በጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በሚገኘው አቅርቦትና ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ መሰረት በተቀመጠው የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይቻላል።
- ጨረታው ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክት አቅርቦት እና ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የጃንሜዳ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት 17-06B
ለበለጠ መረጃ፡- 0118-95-98-10 ወይም 0911-69-13-78
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
