Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ከተማ አስተዳደር
  • Address ጎንደር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 092 3235819
  • Website
  • Deadline13 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security300,000.00
  • opening date2025-12-13 00:00:00
  • Categories Construction Works

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት መምሪያ በኮሪደር ልማት የተገነቡ የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማከራየት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የኮንትራት የኪራይ አገልግሎት ውል መውሰድ ይፈልጋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በኮሪደር ልማት የተገነቡ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማከራየት የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት መምሪያ በኮሪደር  ልማት የተገነቡ የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማከራየት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የኮንትራት የኪራይ አገልግሎት ውል መውሰድ ይፈልጋል።

  1. ፒያሳ የቀድሞው ጅንአድ ላይ የተገነባ ትልቅ ፋውንቴን ያለው የህፃናት መጫወቻ እና ካፌ፣የአዋቂዎች ካፌ፣ የፓርኪንግና ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀር ያለው የመዝናኛ ቦታ በሎት 01
  2. አጼ ፋሲለደስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ የተገነባ ሶስት ቦታ ላይ ፋውንቴን ያለው የካፌ እና የመዝናኛ አገልግሎት ቦታ በሎት 02
  3. ጅቲ ኮሌጅ መግቢያ በር አካባቢ የተገነባ የህፃናት መጫወቻ፣ ክፍት ሲኒማ ማሳያ (Open Cinema) እና የካፌ አገልግሎት መዝናኛ ቦታ በሎት 03
  4. ከ "ራስ እንግዳ” እስከ “ደጃዝማች አለሜ” ፋውንቴን ያለው ክፍት የህዝበ መዝናኛ ቦታ (Public area) እና የካፌ አገልግሎት በሎት 04
  5. ጎንደር መምህራን ኮሌጅ መግቢያ በር በቀኝ በኩል እስከ “የአርበኛ ልጅ" የፓርኪንግና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ አገልግሎት መስጫ ያለው የካፌ አገልግሎት እና የመዝናኛ ቦታ በሎት 05
  6. ጎንደር መምህራን ኮሌጅ መግቢያ በር አካባቢ “ፊታውራሪ ገብርየ“ የካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት እና የመዝናኛ አገልግሎት በሎት 06

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ የሚመለከተው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  4. ስለመዝናኛ ቦታዎች አጠቃላይ መረጃ እና ስለሚሰጡት የአገልግሎት አይነት ዝርዝር መግለጫቸው /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ20/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 04/04/2018 ዓ/ም ድረስ በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከጎንደር ከተማ አስ/ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 21 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 300,000.00/ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከፖስታው ውስጥ ማስገባት
  7. ጨረታው ከ20/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከጎንደር ከተማ አስ/ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 06/04/2018 ዓ/ም ጧት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በመምሪያው ግዥና ፋ/ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር-23 በ06/04/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
  9. አሸናፊ የሚለየው በተወዳደረበት ሎት ለወርሃዊ ኪራይ አገልግሎት በሞላው ከፍተኛ ዋጋ ነው።
  10. የጨረታ አሸናፊው ለመዝናኛ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ቦታውን የሚመጥኑ ጥራት ያላቸውን ሌሎች ተጨማሪ ግብአቶችን አሟልቶ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ጥራታቸውም መ/ቤቱ በሚመድበው ባለሙያ አማካኝነት የሚፈተሽ እና የሚረጋገጥ ይሆናል።
  11. ለአሸናፊ ድርጅቱ እንደአስፈላጊነቱ ሊራዘም የሚችል የሁለት (2) ዓመት የኪራይ አገልግሎት ውል የሚሰጠው ይሆናል።
  12. ነጻ የህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ የተገነቡ ክፍት የመዝናኛ ቦታዎች ባሉበት ሎት (ሎት 04) አሸናፊ የሚሆን ድርጅት ማህበረሰቡ ያለክፍያ የመዝናናት መብቱን ባከበረ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚገደድ ሲሆን የመዝናኛ ቦታውን ዕዳት እና አጠቃላይ ደህንነት በመጠበቅ በሃላፊነት ማስተዳደር ይጠበቅበታል።
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918712038 ወይም በ 0996648851 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስ.ቁ -0918712038/ 0918712038

ጎንደር፣

 

የጎንደር ከተማ አስተዳደር

Save Tender