በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የወረዳው ፍርድ ቤት ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የወረዳው ፍርድ ቤት ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁም መሠረት :-
- እስከ GC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በBC ለሚወዳደር ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ያለው መሆንና የበጀት ዓመቱ የታደሰ የኮንስትራክሽን የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት መሆን ይኖርበታል፣
- ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ ቲን ነምበር ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ኦን ላይን የተመዘገበና ከሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 270,000.00 (ሁለት መቶ ሰባ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ከሚያቀርቡት ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማጎተም ማስቀመጥ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ማለትም 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል እና 2 ቅጂ፣ 1 ቴክኒካል ኦርጂናል እና 2 ቅጂ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዢ/ን/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁ.2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፤
- ጨረታው በ 31ኛው ቀን በ05:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡30 ሰዓት ላይ በደቡብ ሶዶ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግዢና ፋይናንስ ቢሮ ላይ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቶች (ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይታገድም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ /የሕዝብ በዓል/ ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዳቸው ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ግ/ን/አ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በቀድሞው በ2010 በወጣው መመሪያ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ /Arthimetic Error/ ከ 2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር /+251/ 046 - 322 - 8009 ደውለው መጠየቅ ይችላል።
ማሳሰቢያ
- የሕንፃው ግንባታ የሚከናወንበት ቦታ ተጫራቾች ከፍ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ቦታውን መጎበኘትና መጎብኘታቸውን የሚያስረዳ መረጃ ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ልብ ይበሉ - ተወዳዳሪዎች የምታስገቡት ሰነድ የተጭበረበረ /ፎርጅድ/ fraudulent/ ዶክመንት ከሆነ ከጨረታ ወጭ ተደርጎ ተገቢውን ሕጋዊ ርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳስባለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት
