Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0923403764
  • Website
  • Deadline20 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Security400,000.00 (አራት መቶ ሺህ) ብር
  • opening date2025-12-20 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፍ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን G+1 እና ሌሎች ህንፃ ለማስገንባት በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፍ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2018

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፍ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን G+1 እና ሌሎች ህንፃ ለማስገንባት በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት፡-

  1. BC4/GC5 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና በ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ።
  3. ከመንግሥት የሚፈልግበትን የግብር እና የታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከታክስ አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
  • በክልሉ እና በዞን የግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ፤ ውል ያላቋረጡ፤ ተቋራጮችን እየጋበዘ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተቋራጮች የማይመለስ 600 (ስድስት መቶ) ብር በፕሮጀክቱ ስም ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ክፍል ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዘው በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ የጨረታውን ሠነድ ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ሥራ ክፍል መውሰድ ይቻላል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በየብቻ አድርገው ኤንቨሎፕ በማሸግ በእያንዳንዱ ላይ ማህተሙንና ፊርማውን በማሳረፍ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሠነድ እያንዳንዱ በተናጠል በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ22ኛው ቀን በ4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ክፍሎች በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥሉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  • በኦርጅናል ሠነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፈ ይኖርበታል።
  • እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለ120 ቀን ማቅረብ ይኖርበታል።
  • በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሠነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጪ ያደርጋል።
  • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟሉ የሚቀርብ የሥራ ተቋራጭ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
  • በጨረታ ማስታወቂያ የተዘረዘሩ መስፈርቶች ግልጸኝነት ከጎደለው የጨረታ ሠነድ ውስጥ የተጠቀሱ መስፈርቶች ገዥ ይሆናል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፍ/ቤት ፋይናንስ ሥራ ክፍል

በተጨማሪ መረጃ 0923403764 ወይም 0933613334/ 0463313425

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፍ/ቤት

Save Tender