Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
  • Address ይ/ዓለም ከተማ: ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916-406737
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security200,000.00
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Construction Works

በሀዲያ ዞን የዞን ፋ/ኢኮ/ል/መምሪያ የዞኑን የጤና መምሪያ የአጥር ፣ የጥበቃ ቤት እና መሰል ግንባታ ሥራዎችን ለማሠራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዲያ ዞን የዞን ፋ/ኢኮ/ል/መምሪያ የዞኑን የጤና መምሪያ የአጥር ፣ የጥበቃ ቤት እና መሰል ግንባታ ሥራዎችን ለማሠራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1. ደረጃቸው BC-6/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፥ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE LETTER ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃ ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል እንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ግራፊከ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና የፕሮጀከቱን ስም ጠቅሶ እንዲሁም የቴከኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች ኦርጂናል ቴከኒካል ሃሳብ የያዘ ሰነድ (BIDDER CERTIFICATON OF COMPLIANCE ) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴከኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፐሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረቡ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይበተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፈደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናል የቴከኒካል ሃሳብ የያዘ ሰነድ (BIDDER CERTIFCATION OF COMPLIANCE ) በየመጠይቁ (ባዶ ቦታዎች ) ተሞልቶ ተፈርሞና ታሽጎ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሳብ የያዘ ሰነድ ውስጥ የሚገኘውን (BIDDER CERTIFICATION OF COMPLIANCE ) መጠይቆች (ባዶ ቦታዎች) ሳይሞሉ ፈርሞ ማህተም ብቻ አድርጎ መመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡

4. ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዞን ፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡- የተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ግዥ አዋጅ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ከዚህ በፊት በዞኑ ውስጥ ውል ገብተው የግንባታ ሥራ እየሠሩ በውል ጊዜ ያለበቂ ምከንያት ያላጠናቀቁ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የተጻፈባቸው የሥራ ተቋራጮች ጨረታው ላይ መሳተፍ አይችሉም።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር፡- 046 555 31 93 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ/ሆሳዕና/

Save Tender