በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የኤፍ/ግ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ለግብርና ጽ/ቤት እና ለአካባቢ ደን ዱር እንስሳት ልማት ጽ/ቤት /በሪድ ፕላስ ፕሮጀክት / በ2018 በጀት ዓመት ፖሊተን ቲዩብ፤ የደን ዘር እና የሩዝ መፈልፈያ ማሽን በግልጽ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የኤፍ/ግ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ለግብርና ጽ/ቤት እና ለአካባቢ ደን ዱር እንስሳት ልማት ጽ/ቤት /በሪድ ፕላስ ፕሮጀክት / በ2018 በጀት ዓመት ፖሊተን ቲዩብ፤ የደን ዘር እና የሩዝ መፈልፈያ ማሽን በግልጽ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ፡-
- ተጫራቶች በዘርፉ የተመዘገበ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መረጃ እና ለደን ዘሩ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ፤ የሙያ ብቃት ሰርተፍኬት እና የዘር ፍተሻ የላብራቶሪ ውጤት ማረጋገጫ ሰነድ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰርተፈኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ለፖሊተን ቲዩብ 16,000 ብር፣ ሎት 2 ለደን ዘር 7,000 ብር እና ለሩዝ መፈልፈያ ማሽን 10,000 ብር እና ከዚያ በላይ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታው መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት ወይም ሕጋዊ ውክልና ያለው አካል ኦርጅናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ሁሉንም ዕቃዎች በየሎት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በኤፍ/ግ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ19/3/2018 ዓ.ም እስከ 3/4/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም በ5/4/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ለወሰዱት የተጫራች መመሪያ የጨረታ ሰነድ/ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በየሎቱ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው አሸናፊ ስለሚሆን ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሙሉ በሙሉ ጨረታው ላይ ዋጋ መሙላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች እያንዳንዱን ዕቃ በሚፈለገው የጽ/ቤት ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ አለበት። ገቢ ላደረገበት ዕቃ ሞዴል 19 በመያዝ ክፍያ ይፈፀምለታል፡፡
- ጽ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የፖሊተን ቲዩብ ናሙና የምናቀርብ ስለሆነ በናሙናው መሰረት፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል።
ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ቁጥር፡- 0336610319 ወይንም 0911935927 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ። ፖሊተን ቲዩብ የቀረበውን ሳምፕል በማየት መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት
