በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት የከተማ ልማት ሥራዎችን ማለትም የዓ/ከ/ከ/አስ/ከ/መል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚያስገነባው የከተማ ኮሊደር መንገድ ቴራዞ ንጣፍ ግንባታ እና መብራት ዝርጋታ ሥራ ግዥ ለመፈፀም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሥ/ተቋራጭ ከሕንፃ እና ከውሃ ሥራ ተቋራጭ በስተቀር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት የከተማ ልማት ሥራዎችን ማለትም የዓ/ከ/ከ/አስ/ከ/መል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚያስገነባው የከተማ ኮሊደር መንገድ ቴራዞ ንጣፍ ግንባታ እና መብራት ዝርጋታ ሥራ ግዥ ለመፈፀም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሥ/ተቋራጭ ከሕንፃ እና ከውሃ ሥራ ተቋራጭ በስተቀር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በየዘርፉ ላሉት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው።
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/የሥ/ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ ብር በቁርጥ 40,000 ብር (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ገቢ መሰብሰቢያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ18/3/2018ዓ/ም እስከ 2/4/2018 ዓ/ም ድረስ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የጨረታውን አይነት በመግለጽ በፖስታው ላይ በመፃፍና የድርጅቱን ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና ፊርማ በመፈረም ማስታወቂያው ከወጣበት ከ18/3/2018 ዓ.ም እስከ 3/4/2018 ዓ.ም የካላንደር መቁጠሪያ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመምጣት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም በ3/4/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
12. ጨረታው በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 3/4/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ 14 ይከፈታል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 32 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 13 20 801 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
15. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሙሉ ሥራ የመሥራት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
16. የጨረታ መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይቀየራል፡፡
17. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ከቫት በፊት ከነቫቱ እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ በሌለው መልኩ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
18. ተጫራቾች ለሚገዙት ሰነዶች ከቀረበው የግንባታ ሥራ ሰነድ ጋር አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የሥራ ቦታ ዓለም ከተማ
አድራሻ ዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር/ገ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0111320801 / 395
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት
