Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-26 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያስራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ቁጥር ተቋ001/2018 ዓ.ም

 

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያስራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ዘርፍ የተደረጁ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

 

ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 

ሎት

የስራው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

የጨረታ ሰነዱ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

ሎት-1

የወረዳ 01 አርቴፊሻል ሜዳ

100,000 ብር

በጥቃቅንና አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2፡30-10፡00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ

ሎት-2

ብሔራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እድሳት ጂ+0 ማስፋፊያ

100,000 ብር

በጥቃቅንና አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2፡30-10፡00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

  1. በዘርፉ የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  3. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ላይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡00 ድረስ ከተራ ቁ.1-3 ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (orginal) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቀርበው ሠነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ22 ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ለ90 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ በባንከ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (UnConditional Bank Guarantee) ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በግንባታና በዲዛይን በንዑስ ተቋራጭነት ለማሳተፍ የወጣውን መመሪያ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም የሚያሳትፉትን የስራ ዝርዝሮች በመጥቀስ ከስምምነት ደብዳቤ ጋር አያይዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (Construction to Bidder (ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ።
  10. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡ በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
  11. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፈርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአራዳ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ባለሙያዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሰሩ ወይም ለድርጅቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ሀላፊ ወይም ተመሳሳይ ተግባር እና ስልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀጣሪው ባለሙያ የተፈረመ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ ባለሙያ ከአንድ ስራ ተቋራጭ በላይ ፈርሞ ከተገኘ ያስፈረሙት ስራ ተቋራጮች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል፡፡
  15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ጽ/ቤቱ ባወጣው የግንባታ ጨረታዎች ከአንድ ፕሮጀክት በላይ መግዛት የሚቻል ሲሆን መጫረት የሚፈቀደው በአንድ በመረጡት ፕሮጀክት ብቻ ይሆናል፡፡
  17. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው ተከታታይ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ እስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ባለው ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  18. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ።

 

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት

 

Save Tender